Wednesday, March 31, 2021

ክበብ መተዳደሪያ-ደንብ




 የደብረ ማርቆስ ከተማ
የአማርኛ ቋንቋና ሥነ-ጽሁፍ መምህራን ክበብ መተዳደሪያ-ደንብ   አዘጋጆች፡-
Ø  አቶ ግርማው አሸብር
                                                     
  ጥር 2008ዓ/ምደብረ ማርቆስ፣ኢትዮጵያ፤





የደብረ ማርቆስ ከተማ
የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ክበብ
መተዳደሪያ-ደንብ
አንቀጽ 1፣ ስያሜ እና ዓላማ
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና በደብረ ማርቆስ ከተማ ት/ጽ/ቤት ትብብር ‹‹የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ክበብ›› በሚል ስያሜ ተቋቁሟል፡፡ የክበቡ ዓላማ ከአንደኛ ክፍል እስከ መሰናዶ የትምህርት ደረጃ ድረስ የሚሰጠው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በመማር ማስተማሩ ሂደት ያሉበትን ችግሮች በመቅረፍ፣ የቋንቋ ትምህርቱን ዓላማ ማሳካት ነው፡፡ 

አንቀጽ 2፣ ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያስጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ህገ ደንብ ውስጥ፡-
1.  ‹‹አቋመክ›› ማለት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ክበብ ማለት ነው፡፡
2.  ‹‹ጠቅላላ ጉባዔ›› ማለት ጠቅላላ አባላት ማለት ነው፡፡
3.  ‹‹ስአኮ.›› ማለት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማለት ነው፡፡
 
አንቀጽ 3፣ የክበቡ ስልጣንና ተግባር
ክበቡ በዚህ ህገ ደንብ መሰረት የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
1.  በክበቡ ስም ውል የመዋዋል፣
2.  የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንበረትን በባለቤትነት መያዝና በስጦታ መቀበል፣
3.  የባንክ ሂሣብ መክፈት፣
4.  ክበቡ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ስራዎችን የመስራት መብት ይኖረዋል፡፡
አንቀጽ 4፣ የክበቡ ልሳን
ክበቡ የራሱ የሆነ ልሣንና መፅሔት ሌሎችም የሕትመት ውጤቶች የሚኖሩት ሲሆን፣ የልሳኑ ስያሜ “የአማርኛ ድምፅ” የሚል ነው፡፡

አንቀጽ 5፣ የክበቡ ዓርማ
ክበቡ የራሱ የሆነ መለያ አርማ ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ 6፣ አባልነት
ለሙሉ አባልነት የሚያበቃቸውን መመዘኛ አሟልተው በክበቡ የተወሰነውን መብትና ግዴታ የተቀበሉ የክበቡ አባላት ሙሉ አባል ይባላሉ፡፡

አንቀጽ 7፣ ለሙሉ አባልነት የሚያበቁ ሁኔታዎች
ለሙሉ አባልነት የሚያበቁ መመዘኛዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.  የአማርኛ ቋንቋ መምህር መሆን፤
2.  በአማርኛ ቋንቋ እና በቋንቋው ትምህርት ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚፈልግ እና የክበቡ አባል ለመሆን ሙሉ ፍላጐት ያለው፤
3.  የክበቡ ዓላማ ግቡን እንዲመታ በየደረጃው ባሉ የስራ እርክኖች ገብቶ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን እና ሌሎች በክበቡ የውስጥ ደንብ የሚደነገጉ መተዳደሪያ ደንቦችን መቀበል ናቸው፡፡

አንቀጽ 8፣ የክበቡ አባላት የሚከተሉት መብቶች ይኖሯቸዋል፡-
1.  በሁሉም የክበቡ ጉባዔዎች መገኘትና ይወክለኛል የሚሉትን አባል በክበቡ ደንብና መመሪያ መሠረት ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴነት መምረጥ፤ መመረጥ፤
2.  ክበቡ በሚያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ተግባራት፣ መድረኮች፣ወዘተ. መሳተፍ፣ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በነፃ የመግለጽና በማንኛውም የክበቡ የስራ እንቅስቃሴ ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን በማቅረብ መገምገም፣
3.  ስለክበቡ የስራ እንቅስቃሴ መረጃ መጠየቅና ማግኘት፣
4.  ክበቡ ከሚሠራቸው ስራዎች ተጠቃሚ መሆን፣
5.  መብታቸውንና ነፃነታቸውን የሚጋፉ ተግባራት ሲፈፀሙባቸው በክበቡ አቅምና መመሪያ መሠረት ድጋፍ የማግኘት እድል ይኖራቸዋል፡፡

አንቀጽ 9፣ የክበብ አባልነት ግዴታ

  የክበቡ አባላት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሯቸዋል፡፡
1.  ለክበቡ ዓላማ፣ እቅድና ህግ ተግባራዊነት ተገዠ መሆን፣
2.  የክበቡ ጉባዔ የወሰነውንና የሚወስነውን የአባልነት ክፍያ ወይም መዋጮ መክፈል፣
3.  ክበቡ በሚሠራቸው የትምህርት፣የስልጠናና የምርምር የስራ እንቅስቃሴዎች መሳተፍ፣
4.  የክበቡ ዓላማ በሌሎች ዘንድ ይበልጥ እንዲታወቅ መጣር፣

ንቀጽ 10፣ የውሳኔ አሰጣጥ
1.  የክበብ አባል የሆነ ማንኛውም መምህር በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በነጻ የመወያየትና የመከራከር መብቱ ያለገደብ የተጠበቀ ነው፣
2.  ለክበቡ አባላት ለውይይት የቀረበ የመወያያ ርዕስ በቂ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ ውሳኔ ይሰጥበታል፣
3.  ውሳኔዎች በስብሰባው ላይ በተገኙ በክበቡ አባላት 2/3ኛ ድምጽ ይተላለፋሉ፡፡

አንቀጽ 11፣ የክበቡ የገቢ ምንጭ
ክበቡ የሚከተሉት የገቢ ምንጮች ይኖሩታል፡-
  1. ከአባላት መዋጮ በመሰብሰብ፣
  2. የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን በመስራት፣
  3. ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ ድጋፍ፣
  4. ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ  የሚገኝ ድጋፍ፣
  5. ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ከሚሰጥ ድጋፍ፣
  6. ከደብረ ማርቆስ  ከተማ አስተዳደደር ትምህርት ጽ/ቤት ከሚሰጥ ድጋፍ፣
  7. የክበቡን መመስረት ከሚደግፉ ተቋማትና ግለሰቦች፣
  8. ከምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ት/ጽ/ቤት ከሚገኝ ድጋፍ፣
  9. ለቋንቋው እድገት ከሚሰሩ ድርጅቶች፣
10. ክበቡ ከሚያቋቁማቸው የተለያዩ የገቢ ምንጮች የሚገኝ ገንዘብ ወዘተ. ይሆናል፡፡

አንቀጽ 12፣ የክበቡ አወቃቀር
1.  አቋመክ ተጠሪነቱ ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና ለደብረ ማርቆስ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሲሆን በስሩ የተለያዩ ዘርፎች ይኖሩታል፣ 
2.  በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አቋመክ እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ዘርፎችን በትምህርት ቤቶቹና በዩኒቨርሲቲው ግቢ ማቋቋም ይችላል፣

አንቀጽ 13፣ የክበቡ አጠቃላይ አደረጃጀት
የአቋመክ አደረጃጀት እንደሚከተለው ይሆናል፡-
1.  የአቋመክ ክበብ ጠቅላላ ጉባዔ
2.  ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣
3.  የክበቡ በሥሩ የተቋቋሙ ዘርፎች፣
4.  የት/ቤቶች ክበብ ተጠሪ

አንቀጽ 14፣ ጠቅላላ ጉባዔ
ጠቅላላ ጉባዔው ተጠሪነቱ ለክበቡ አባላት ሆኖ ከሁሉም ት/ቤቶች በምርጫ የተወከሉ አባላትን የያዘ ነው፡፡

አንቀጽ 15፣ የጠቅላላ ጉባዔ ስልጣንና ተግባር
የ‹‹አቋመክ›› ጠቅላላ ጉባኤ በዚህ ህገ ደንብ መሰረት የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፡፡
1.  አቋመክ የሚመራባቸውን ደንቦች መመሪያና ስልቶች ያፀድቃል፣ያሻሽላል፣
2.  የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን ዘገባ ያዳምጣል፤ ያፀድቃል፤ አስፈላጊ ናቸው የሚላቸውን ውሳኔዎች ያሳልፋል፤ እስከ ቀጣዩ ጉባዔ ድረስ የሚሰሩ ስራዎችን መርጦ ያፀድቃል፣
3.  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የክበቡን ደረጃ፣ ስም፣ መዋቅርና አደረጃጀት መለወጥ የሚያስችል ስልጣን ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ 16፣ መደበኛ ስብሰባ
1.  የክበቡ መደበኛ ስብሰባ በየወሩ አንድ ጊዜ ይካሄዳል፡፡
2.  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በስራ አስፈፃሚው፣ በጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ ወይም የክበቡ አባላት ጥያቄ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፣

አንቀጽ 17፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስራና ኃላፊነት
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ስራና ሃላፊነት ይኖሩታል፡-
1.  የክበቡን ስራ ይመራል፣
2.  በጠቅላላ ጉባዔ የፀደቁ እቅዶችን ያስፈጽማል፣
3.  በየዘርፉ ያሉ የተቋቋሙ አካላት በበላይነት ይመራል የስራ ዘገባ ይቀበላል የሰው ኃይል አደረጃጀት በሚመለከት ውሳኔ ይሰጣል ለጠቅላላ ጉባዔው ዘገባ ያቀርባል፣
4.  የየዘርፍን ስራና ኃላፊነት በውስጡ ላሉት አባሎች ያከፋፍላል፣
5.  የክበቡን ሂሳብ የሚያንቀሳቅሱ ሰዎችን ይወክላል፣
6.  በየወሩ ይሰበስባል፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፣

አንቀጽ 18፣ የስራ ዘመን
የ“አቋመክ›› ክበብ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አንድ የስራ ዘመን ሦስት ዓመት ነው፡፡
አንቀፅ19፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት
1.  ሰብሳቢ
2.  ምክትል ሰብሳቢ
3.  ጸሐፊ
4.  ገንዘብ ያዥ
5.  ሂሳብ ሹም
6.  ህዝብ ግንኙነት
7.  አንድ አባል ናቸው፡፡

አንቀጽ 20፣ የሊቀመንበር ሥራና ኃላፊነት
“የአቋመክ›› ክበብ ሊቀመንበር ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔ ሆኖ የማከተሉት ስራና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-
1.  ጠቅላላ ጉባዔውንና ስራ አስፈፃሚ ኮማቴውን በበላይነት መምራት፤
2.  የክበቡን የስራ አፈጻፀም መከታተል
3.  የየዘርፉን የስራ አፈጻፀም  ዘገባ አጠናቅሮ ለጠቅላላ ጉባዔው ማቅረብ፤
4.  ክበቡን በመወከል ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ግንኙነት ማድረግ፤
5.  በክበቡ ስም ውሎችንና ስምምነቶች መፈረም፤
6.  ሥራዎችን ለየዘርፉ ማከፋፈል፣ አፈፃፀሙን መከታተል፣
7.  በጠቅላላ ጉባዔው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ማከናወን ናቸው፡፡

  ንቀጽ 21፣ የምክትል ሊቀመንበሩ ስልጣንና ተግባር
ምክትል ሊቀመንበሩ ተጠሪነቱ ለሊቀመንበሩና ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሆኖ፡-
1.  ሊቀመንበሩ በማይኖርበት ወይም ስራውን ለማከናወን በማይችልበት ጊዜ ተተክቶ ይስራል፤
2.  በሊቀመንበሩ ተለይቶ የሚሰጠውን ተግባራት ያከናውናል፤
3.  በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚሰጠውን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
አንቀጽ 22፣ የፀሐፊው ስልጣንና ተግባር
ፀሐፊው የሚከተሉት ስራና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-
1.  የክበቡን ጽ/ቤት በበላይነት ይመራል፤
2.  በክበቡ መተዳደሪያ ደንብ፣ መመሪያና አግባብ ባላቸው ሌሎች መመሪያዎች እየተመራ ሌሎች ኮሚቴዎችን ይከታተላል፤
3.  የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዩች ሲኖሩ ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በማቅረብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፤
4.  የክበቡን የስራ ዘገባ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቃለ-ጉባዔና መረጃዎችን በአግባቡ ተይዘው እንዲቀመጡ ያደርጋል፤
5.  በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

አንቀፅ 23፣ ገንዘብ ያዥ
1.   ተጠሪነቱ ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው፡፡
2.   የማህበሩን ገቢና ወጭ በሚመለከት ከሰብሳቢው ጋር በመሆን ይሰራል፡፡
3.   ክፍያ ያላጠናቀቁ አባላትን ተከታትሎ እንዲከፍሉ ያደርጋል፡፡

አንቀፅ 24፣ ሂሳብ ሹም
1.   የማህበሩን ገንዘብ ገቢና ወጭ ይቆጣጠራል፡፡
2.   የማህበሩን ገንዘብ ቢንስ በዓመት አንድ ጊዜ እየመረመረ የስራ አፈፃፀምን ሪፖርት
ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀርባል፡፡

አንቀፅ 25፣ ህዝብ ግንኙነት
  1. ተጠሪነቱ ለክበቡ ሰብሳቢ ሆኖ ክበቡን የሚያስተዋውቁ በራሪ ፅሁፎችን፣ መፅሄቶችን እና የመሳሰሉትን ያዘጋጃል፣ ያሰራጫል፣
  2.  የክበቡ ስራ በተመለከተ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፣
  3.  ዜናዎችን፣ መጣጥፎችንና ማስታወቂያዎችን በማዘጋጀት ለትምህርት ቤቶች፣ ለትምህርት ቢሮ፣ ለትምህርት ጽ/ቤት፣ለመገናኛ ብዙሃን፣ ወዘተ. በመላክ የክበቡ ስራዎች ሳውቃል፣
  4.  ለክበቡ ድረገፅ በማዘጋጀት የክበቡን እንቅስቃሴዎች ይዘግባል፡፡    
አንቀጽ 26፣ የጋራ ስራና ኃላፊነቶች
1.  የ“አቋመክ›› ሊቀመንበር፣ ዋና ፀሃፊ እና ሂሳብ ሹም በክበቡ የሂሳብ ደብተር ላይ በጋራ ይፊርማሉ፤
2.  የክበቡን ሂሳብ ለማንቀሳቀስ ሂሳብ ሹም፣ሊቀመንበርና ፀሃፊ እንዲፈርሙ ይደረጋል፤ ሊቀመንበሩ በማይኖርበት ጊዜ በሂሳብ ሹሙና በፀሃፊው ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡
3.  በክበቡ ስር የሚገኙ የተለያዩ ዘርፎችን ተከፋፍለው በግል ይመራሉ፣ በህብረትም ያስተዳድራሉ፡፡
አንቀጽ 27፣ የ“አቋመክ›› ልዩ ልዩ ክፍሎች
‹‹አቋመክ›› ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያግዙ በሊቀመንበሩ፣ በምክትል ሊቀመንበሩና በዋና ፀሐፊው በበላይነት የሚመሩ የሚከተሉት የስራ ክፍሎች ይኖሩታል፡-
1.  የገቢ አፈላላጊ ዘርፍ፣
2.  የህዝብ የግንኙነት ዘርፍ፣
3.  የጥናትና ምርምር ዘርፍ፣
4.  የትምህርትና ስለጠና ዘርፍ፣
5.  የስነጽሁፍ ዝግጅት ዘርፍ፣
6.  የንባብ  ዘርፍ፣
7.  የውይይትና የክርክር ዘርፍ
8.  የመድረክ አዘጋጅ ዘርፍ፣
9.  የልምድ ልውውጥ ዘርፍ፣
10. የመረጃ አሰባሳቢ ዘርፍ ናቸው፡፡

አንቀጽ 28፣ የገቢ አፈላላጊ ዘርፍ ኃላፊነት

የገቢ አፈላላጊ ዘርፍ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
1.  የማህበሩን አቅም የሚያሳድጉ ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች እንዲቀረፁ ማድረግና መከታተል፤
2.  የክበቡን የንብረት አስተዳዳር መከታተል፤
3.  የክበቡን የገቢ ምንጭ የሚያጐለብቱ እንቅስቃሴዎች መፍጠርና መተግበር፤
4. አቅም በፈቀደ መጠን የክበቡ አባላት ኢኮኖሚያዊ እና ሙያዊ አቅማቸውን የማያሳድግ ስልጠናዎች እንዲያገኙ ማድረግ፣ የተገኙ ለውጦችንና እድገቶችን መከታተል፡፡

5. አንቀጽ 29፣ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ስራና ኃላፊነት

የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
1.  ክበቡ ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ክበባት፣ ማህበራትና ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ለማድረግ የሚችልበትን ሁኔታ መፈጠር፤
2.  በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ በተመሳሳይ  ከሚሰሩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ድርጅቶች ጋር በህብረት የሚሰራበትን መንገድ ማመቻቸት፤
3.  የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትና መምህራንን የሚመለከቱ የተዛቡ አሰራሮች ሲኖሩ  እንዲሻሻሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ተፈጻሚነት እንዲያገኝ ማድረግ፤
4.  የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም የክበቡን እንቅስቃሴ ለህዝብ እንዲታወቅ ማድረግ፤
5.  የክበቡ አባላትና ሌሎች ተማሪዎችና መምህራን መብታቸውን ግዴታቸውን የተመለከቱ ህጐችንና ደንቦችን እንዲያውቁ ጥረት ማድረግ፤

አንቀጽ 30፣ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ስራና ኃላፊነት

የጥናትና ምርምር ዘርፍ የሚከተሉት ስለጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
1.  የአማርኛ ቋንቋን፣ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን፣ በመሳሰሉት ላይ ትኩረት ያደረጉ ምርምርና ጥናቶች እንዲካሂዱ ያግዛል፣ ወጭዎችን ይሽፍናል፤ የሚሸፍን አካል ያፈላልጋል፡፡
2.  የአማርና ቋንቋ መድብለ ቃላትን፣ ስነቃሎችን፣ ወዘተ. ያሰባስባል/ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፡፡
3.  ክበቡ በሚሰራባቸው ሰራዎች የመጡትን ለውጦች በሚመለከት ጥናት ያካሂዳል፣ እንዲካሄድ ያደርጋል፤
4.  ክበቡን ለማሳደግ የሚያግዙ ጥናቶች ያካሂዳል፣ እንዲካሄዱ ያደርጋል፤
5.  ክበቡ ከመግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት በቀጣይነት እንዲያድግ ለማድረግ ስለሚኖረው እንቅስቃሴ ጥናት ያካሂዳል፤ እንዲካሄድ ያደርጋል፤
6.  ጥናቶችን በህትመት መልክ በማዘጋጀት ያሰራጫል፤
7.  ጥናቶቹ ወደ ትምህርት ቤቶችና ህዝብ የሚደርስበት መድረክ ያዘጋጃል፡፡

አንቀጽ 31፣ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ

የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የሚከተሉት ስለጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
1.  በክበቡ ውስጥ ዓላማውን የሚመለከቱ ረጅምና አጫጭር ስልጠናዎችንና ትምህርቶችን ያዘጋጃል፤
2.  የትምህርት እድሎችን ለአባልትና ለተጠቃሚዎች ያፈላልጋል፤
3.  በዘርፉ ጥሩ ውጤት ላሳዩ ፣ድጋፍ ለሰጡ፣ ተምሳሌት ለሆኑ ሽልማት ያዘጋጃል፤ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
4.  በክበቡ ለሚሰጡ ትምህርቶች ማስተማሪ መሳሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ያደራጃል፣ ያሰራጫል፤
5.  በክበቡ የተቋቋሙ የትምህርትና ስልጠና ዘርፎችን ይከታተላል፤ ያስተዳድራል፡፡

 አንቀፅ 32፣ የስነ-ጽሁፍ ዝግጅት ዘርፍ

የስነጽሁፍ ዘርፍ የሚከተሉት ስለጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
1.  የክበቡ አባላት የስነፅሁፍ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት አጫጭር ስልጠናዎችን ያመቻቻል፤
2.  የክበቡ አባላት የስነፅሁፍ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና በባለሙያ እንዲገመገም ያደርጋል፤
3.  የክበቡ አባላት የስነፅሁፍ ስራዎቻቸውን ለህዝብ የሚያቀርቡበት መድረክ ያዘጋጃል፤
4.  በክበቡ አባላት የተዘጋጁ የስነፅሁፍ ስራዎች የሚታተሙበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡

አንቀፅ 33፣ የንባብ ዘርፍ
የንባብ ዘርፍ የሚከተሉት ስለጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
1.  የንባብ ቦታንና ጊዜ መርጦ ያዘጋጃል፤
2.  ተማሪዎችን በየደረጃቸው በመመደብ የንባብ የጊዜ ሰሌዳ ያዘጋጃል፡፡
3.  የሚነበቡ መፅሀፍትን/ ፅሁፎችን ያፈላልጋል፣ በስጦታ ይቀበላል፣ መርጦ ያዘጋጃል፤
4.  የንባብ መከታተያ መልመጃዎችን ያዘጋጃል፣ ለተማሪዎች ያሰራጫል፤
5.  የክበቡን አባላት እና ሌሎች ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች የንባብ ጊዜ ሰሌዳ በማውጣት  እንዲመሩ ይመድባል/ይጋብዛል፡፡

አንቀፅ 34ውይይትና የክርክር ዘርፍ
የውይይትና የክርክር ዘርፍ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
የዚህ ዘርፍ ዓላማ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ የንግግር ችሎታቸውን በማዳበር አንደበተ ርቱዕ ደረጃ የሚደርሱበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
1.  ተማሪዎችን የሚያወያዩና የሚያነጋግሩ ርዕሰ ጉዳዮችን በማቅረብ ውይይት የሚያደርጉባቸውን መድረኮች ማዘጋጀት (የሚመረጡት ርዕሰ ጉዳዮች እግረመንገዳቸውን የተማሪዎችን አስተሳሰብ የሚገነቡ መሆን አለባቸው)፣
2.  ተማሪዎችን የሚያከራክሩ ርዕሰ ጉዳዮችን በመምረጥ ክርክር የሚያደርጉበትን መድረኮች ማዘጋጀት (ለክርክር የሚመረጡት ርዕሰጉዳዮች እግረመንገዳቸውን ተማሪዎችን የሚያስተምሩ መሆን አለባቸው)፣
3.  የተማሪዎችን የአማርኛ ቋንቋ ችሎታ በማዳበር ላይ ያተኮሩ ውይይትና ክርክር ለማድረግ የሚያስችሉ መመሪያዎች ማዘጋጀትና ለተማሪዎች ማሳወቅ፣

አንቀፅ 35፣ የልምድ ልውውጥ ዘርፍ

የልምድ ልውውጥ ዘርፍ የሚከተሉት ስለጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
1.  በአማርኛ ቋንቋ መምህርነት ረጅምም ሆነ ጥቂት የስራ ልምድ ያላቸውንና ስኬታማ የተባሉ አርአያ መምህራንን በመምረጥ ልምዳቸውን የሚያካፍሉበትን መድረክ ማዘጋጀት፣
2.  በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አሰጣጥና ውጤት በማስመዝገብ መልካም ልምድ ያላቸውን ትምህርት ቤቶችና ተቋማት በመለየት በት/ቤት ደረጃ የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ ማመቻቸት፣
3.  አርአያ የሆኑ መምህራንና ት/ቤቶችን ልምድ በተመለከተ አጫጭር ጽሁፎችን በማዘጋጀት በበራሪ ጽሁፍ፣ በመፅሄት፣ በጋዜጣ፣ወዘተ እንዲወጣ ማድረግ፣ 

አንቀፅ 36፣ የመድረክ አዘጋጅ ዘርፍ
የመደረክ አዘጋጅ ዘርፍ የሚከተሉት ስለጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
1.  የጉባዔ ተሳታፊዎችን ብዛት ይወስናል፣
2.  የጉባዔውን ቦታና ጊዜ ወስኖ ያስታውቃል፣
3.  የጉባዔውን መወያያ ነጥቦች ለጉባዔው የሚቀርቡ ተግባራትን ይወስናል፣

አንቀፅ 37፣ የመረጃ አሰባሳቢ ዘርፍ

የመረጃ አሰባሳቢ ዘርፍ የሚከተሉት ስለጣንና ተግባራት የኖሩታል፡-
1.  በአማርኛ ቋንቋ መማር ማስተማር ሂደት የሚታዩ ችግሮችን ለይቶ ማቅረብ፣
2.  በክበቡ የአሰራር ሂደት የሚከሰቱ ችግሮችን ለይቶ ማቅረብ፣
አንቀፅ 38
ይህን ደንብ በ‹‹አቋመክ›› ጠቅላላ ጉባዔ ቀርቦ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡


የአቋመክ አወቃቀር የሰው ሀይል ምደባ
1.  የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
ሰብሳቢ


ም/ሰብሳቢ


 ጸሃፊ


ገንዘብ ያዥ


ሂሳብ ሹም


ህዝብ ግንኙነት


አባል



2. ልዩ ልዩ ዘርፎች
የዘርፎቹ መጠሪያ
የዘርፉ አባላት
የዘርፉ ተጠሪ
የገቢ አፈላላጊና  የፕሮጀክት ዘርፍ፣


የህዝብ የግንኙነት ዘርፍ፣


የጥናትና ምርምር ዘር


የትምህርትና ስለጠና ዘርፍ፣


የስነጽሁፍ ዝግጅት ዘርፍ


የንባብ  ዘርፍ ናቸው፡፡


የውይይትና የክርክር ዘርፍ


የመድረክ አዘጋጅ ዘርፍ


የመረጃ አሰባሳቢ ዘርፍ


የልምድ ልውውጥ